የሀገር ውስጥ ዜና

ራሱን የጋምቤላ ነፃነት ግንባር ብሎ የሚጠራው ድርጅት ዋና የጦሩ መሪ ሆኖ ሲሰራ የነበረው ግለሰብ ለመንግስት እጁን ሰጠ

By Meseret Awoke

February 24, 2022

አዲስ አበባ የካቲት 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል ራሱን የጋምቤላ ነፃነት ግንባር (ጋነግ) ብሎ የሚጠራው ድርጅት ዋና የጦሩ መሪ ሆኖ ሲሰራ የነበረው ግለሰብ አቶ ዛን ዱዌር በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ለመንግስት እጁን ሰጠ።

ግለሰቡ ቀደም ሲል የክልሉ መንግስት ባደረገው ሰላማዊ ጥሪ ተከትሎ በአካባቢው ጎሳ መሪዎች አማካኝነት ወደ ህዝቡ መመለስ መቻሉ ተጠቅሷል።

የጋምቤላ ነፃነት ግንባር ( ጋነግ) ድርጅት የጦሩ መሪ ሆኖ ሲሰራ የነበረው አቶ ዛን ዱዌር በተሳሳተ መንገድ ወደ ጫካ በመግባት የትጥቅ ትግል ሲያደርግ እንደነበር ተመልክቷል።

መንግስት ያደረገውን የሠላም ጥሪ ተከትሎ ወደ አካባቢው የተመለሰው ግለሠብ ከመንግስት ጋር በመሆን ተገቢው ክትትል እየተደረገ መሆኑን ከክልሉ መንግስት ፕረስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!