በክልሉፕሮጀክት አፈጻጸም ላይ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ለመቅረፍ አመራሩ በቁርጠኝነት ሊንቀሳቀስ ይገባል – ወ/ሮ ሚስራ አብደላ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረሪ ክልል ከፕሮጀክት አፈጻጸም ጋር ተያይዞ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ለመቅረፍ አመራሩ በቁርጠኝነት ሊሰራ ይገባል ሲሉ የሐረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወ/ሮ ሚስራ አብደላ አሳሰቡ፡፡
የሐረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት በክልሉ እየተከናወኑ የሚገኙ ፕሮጀክቶች አፈፃፀምን ተመልክቶ ውይይት በማድረግ አቅጣጫ አስቀምጧል።
ምክትል ርዕሰ መስተዳድሯ በመድረኩ ባስተላለፉት መልዕክት÷ በክልሉ በአንዳንድ ፕሮጀክቶች የአፈፃፀም ላይ ክፍተት የሚስተዋል መሆኑን አብራርተዋል፡፡
በተለይም በክልሉ ከመንገድ ግንባታ እና ከካሳ ክፍያ ጋር ተያይዞ የሚታዩ ችግሮችንና ጥያቄዎች በአግባቡ ምላሽ መስጠት ይገባል ነው ያሉት፡፡
በዚህም በህብረተሰቡ ዘንድ ቅሬታን መፍጠሩን ጠቁመው÷ ክፍተቱን ለመቅረፍ አመራሩ በቁርጠኝነት ሊሰራ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል፡፡
የካቢኔ አባላቱ በበኩላቸው ÷የህዝብን ጥያቄ ሊመልሱ የሚችሉ ፕሮክቶችን ቅድሚያ መስጠትና ማጠናቀቅ እንደሚያስፈልግ አንስተዋል፡፡
በአፈፃፀም ላይ የጎላ ክፍተት ባሳዩ አመራሮች ላይ ተጠያቂነትን በማስፈን እርምጃ መውሰድ እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡
በሚከናወኑ ፕሮጀክቶችም የተጠናከረ ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ አስፈላጊ ነው መባሉን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!