Fana: At a Speed of Life!

የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማና የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች ለአማራ ክልል 40 ሚሊየን ብር የሚገመት ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ እና የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች ለአማራ ክልል በጦርነቱ ለተጎዱ ወገኖች የሚሆን 40 ሚሊየን ብር  የመገመት የአልባሳት፣ የምግብ እና የቢሮ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረጉ።

በድጋፍ ርክክቡ ወቅት የተገኙት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ የአዲስ አበባ ከተማ ህዝብ ኢትዮጵያ ስትነካ እንደማይወድ በጭንቅ ቀን ለአማራ ህዝብ ያደረገው ድጋፍ ማሳያ ነው ብለዋል።

“የሽብር ቡድኑ አማራ እና አፋር ክልሎችን ያወደመው ድንበርተኛ ስለሆንን እንጂ  ዓላማው ኢትዮጵያን ማፍረስ ነው” ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፥ “ፀረ ኢትዮጵያ የሆነውን የሽብር ቡድን ለማጥፋት መላው ኢትዮጵያውያን ከጎናችን ተሰልፈው ከፍተኛ መስዋዕትነት ስለከፈሉ እናመሰግናለን” ብለዋል።

እንደ ሀገር የመጣውን ችግር  በጋራ ለመፍታት ጥረት ስናደርግ ቆይተናል ያሉት ዶክተር ይልቃል፥ ድሉ ዘላቂ እንዲሆን ቀጣይነት ያለው ትግል ማድረግም እንደሚገባ ነው ያመለከቱት።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በበኩላቸው፥  “በህልውና ዘመቻው ጉዳት የደረሰበት የአማራ ክልል ችግሩን ለመፍታት ድጋፋችንን አጠናክረን እንቀጥላለን” ብለዋል።

በአማራ ክልል ባለፉት ጊዜያት 1 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር ድጋፍ የተደረገ ሲሆን፥ ለዚህ ደግሞ የአዲስ አበባ ህዝብ ለኢትዮጵያ ያለውን ክብር ከቃል አልፎ በተግባር በማሳየቱ ምስጋና ይገባዋል ብለዋል።

በጦርነቱ የወደሙ 11 የአማራ ክልል ከተሞችን ለ11 ክፍለ ከተሞች መዘጋጃ ቤቶችን እንደገና ለማቋቋም በትብብር እየተሰራ መሆኑን አንስተውም፥ በጤናው እና በትምህርቱ ዘርፍ ከባለሙያ ጀምሮ በቁሳቁስ  እየተደረገ ያለው ድጋፍ ውጤታማ ሆኗል ነው ያሉት።

የለሚኩራ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ መላኬ አለማየሁ÷ለበርካታ ጊዜያት ህብረተሰቡ የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርግ መቆየቱን አንስተው፥  ዛሬም የንፋስ ስልክ ላፍቶ እና የለሚኩራ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች፣ አርሶ አደሮች፣ ነጋዴዎች፣ ባለሃብቶች እና ወጣቶች የድርሻቸውን መወጣታቸውን ተናግርዋል።

በምንይችል አዘዘው

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.