በትራንስፖርትና ሎጂስቲክ አገልግሎት ዘርፍ ለግል ባለሀብቶች 44 የኢንቨስትመንት ዘርፎች ተዘጋጅተዋል – ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የግል ባለሃብቶችን በትራንስፖርትና ሎጂስቲክ አገልግሎት ዘርፍ ለማሰማራት የሚያስችሉ 44 የኢንቨስትመንት ዘርፎች መዘጋጀታቸውን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክ ሚኒስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ አስታወቁ።
ሚኒስትሯ በትራንስፖርትና ሎጂስቲክ አገልግሎት ፖሊሲና በዘርፉ እየተሰሩ ያሉ ተግባራትን በሚመለከት በቅርብ ለተሾሙ አምባሳደሮች ገለፃ አድርገዋል።
በገለፃቸውም ሚኒስትር መስርያ ቤቱ ኢትዮጵያ በዘርፉ ያላትን ሀብት በሚገባ መጠቀም እንድትችል የማስተዋወቅና ባለሀብቶችን ወደ ሀገር የማምጣት ስራ ላይ አምባሳደሮች በተለየ ትኩረት መስራት እንዳለባቸው ጠይቀዋል።
ወ/ሮ ዳግማዊት ለግል ባለሀብቶች ተለይተው ለተቀመጡ የኢንቨስትመንት አማራጮች ለአንዳንዱ የአዋጭነት ጥናት ተዘጋጅቶ መቀመጡንም ጠቁመዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ በበኩላቸው ባለ ሀብቶችን ወደ ሀገር ለማምጣት በሚደረገው ሂደት ውስጥ ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገባቸው የትራንስፖርት መሰረተ-ልማትና ፖሊሲን አመቺ ለማድረግ የየበኩላችን አስተዋጽኦ ማድረግ ይገባል ማለታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!