Fana: At a Speed of Life!

በ54 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ለሚገነባው የኮሾ መስኖ ፕሮጀክት ሳይት ከተቋራጮች ጋር ርክክብ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በየም ልዩ ወረዳው ሳጃ ከተማ አስተዳደር በ54 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ከሳጃ ላፍቴን ኮሾ ድረስ የሚገነባው የመስኖ ፕሮጀክት ሳይት ከተቋራጮች ጋር ርክክብ ተካሂዷል፡፡

በሳይት ርክክቡ የተገኙት የልዩ ወረዳው ውሃና ማዕድን ኢነርጂ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ጂሀድ ሳንቢ ፥ የኑሮ ውድነቱን ለመቀነስ ግብርናውን ማዘመን እንደሚገባ ገልጸው ፥ ለዚህም የመስኖ ልማት ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ብለዋል፡፡

የክልሉ መስኖ ኤጀንሲ መሀንዲስ አቶ አባይነህ አየለ ፥ በልዩ ወረዳው ለመስኖ ልማት ስራ በ54 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ወጪ በደቡብ ውሃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ተቋራጭነት እና በደቡብ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ድርጅት ጋር በጋራ በመሆን ወደ ስራ እንደሚገቡ ጠቁመዋል ፡፡

ፕሮጀክቱ ከ175 ሄክታር በላይ መሬት ማልማት የሚችል ሲሆን ፥ ከ810 በላይ አባወራና እማወራዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑንም አቶ አባይነህ አየለ አክለው ገልጸዋል፡፡

በሰባት ወራት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ የታቀደው ይህ ፕሮጀክት ግንባታው በተያዘለት የጊዜ ገደብ ተጠናቆ ለህብረተሰቡ አገልግሎት እንዲሰጥ የሁሉም ባለድርሻ አካል ርብርብ ይፈልጋልመባሉን ከደሬቴድ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.