Fana: At a Speed of Life!

የኔዘርላንድስ ኩባንያ በኢትዮጵያ የሚገኙ የእንስሳት ባለሃብቶችን እንደሚደግፍ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣የካቲት 18፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኔዘርላንድስ ኩባንያ የእንስሳት ሀብት ልማት ፕሮጀክት በመጀመር በኢትዮጵያ የሚገኙ የእንስሳት ባለሃብቶችን እንደሚደግፍ አስታውቋል፡፡

አምባሳደር ሂሩት ዘመነ በትላንተናው ዕለት በዓለም ከ40 አገራት በላይ የሚንቀሳቀስውንና ፒኮሊን/ ሺፕፐርስ የተሰኘውን የኔዘርላንድስ ኩባንያ የንግድ ዳይሬክተር ሚስተር ጄሮን ቤይጀርን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው በአዲሱ የእንስሳት ፕሮጅክት ዙሪያ አነጋግረዋቸዋል፡፡

ኩባንያው የእንስሳት ምርትን ለማሳደግ ትኩረት አድርጎ የሚሰራ ሲሆን ኩባንያ ሲሆን፥ ቀደም ሲል ከኢፌዲሪ ግብርና ሚኒስቴር ጋር በእንስሳት ሀብት ዘርፍ የጀመረውን ትብብር ለማጠናከር የሚያስችል የሀሳብ ልውውጥ ማድረጋቸውም ተመልክቷል።

አምባሳደር ሂሩት በዚሁ ጊዜ ባደረጉት ንግግር፥ ኩባንያው ከ160 ሚሊዮን በላይ የእንስሳት ሀብት ባላት ኢትዮጵያ ውስጥ በእንስሳት ሀብት ዘርፍ ለመሰማራት ያሳየውን ፍላጎት አድንቀዋል።

ይህ ፕሮጀክት በተለይ የእንስሳትን የኮንትሮባንድ ንግድ በመከላከልና አነስተኛ የእንስሳት ሀብት ያላቸውን ባለሀብቶች በመደገፍ የዘርፉን የንግድ ቅልጥፍና እንደሚያሳድግ አምባሳደሯ ተናግረዋል።

ሚስተር ቤይጀር በበኩላቸው፥ የእንስሳት የእርባታ አካባቢዎችን ንጽህና በመጠበቅ፣ውጤታማ የእንስሳት አያያዝ ለመፍጠር እና አነስተኛ የእንስሳት ባለንብረቶችን የፋይናንስ አቅም ለማሳደግ ድርጅታቸው በትኩረት እንደሚሰራ መናገራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.