600 ሚሊየን ብር ወጭ የሚደረገበት የወራቤ ኤሌክትሪክ ማከፋፈያ ጣቢያ ግንባታ ተጀመረ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 600 ሚሊየን ብር ወጭ የሚደረገበት እና በአካባቢው ያለውን የኤሌክትሪክ እጥረት እንደሚቀርፍ የታመነበት የወራቤ ኤሌክትሪክ ማከፋፈያ ጣቢያ ግንባታ ዛሬ ተጀምሯል፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የስራና ክህሎት ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል፥ የወራቤ ኤሌክትሪክ ማከፋፈያ ጣቢያ ግንባታ አካባቢውን ብሎም የሀገሪቱን ኢኮኖሚ የሚያግዝ መሆኑንና መንግስትም የገባውን ቃል እንደሚፈፅም ማሳያ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ፕሮጀክቱ በአካባቢው ከኤሌክትሪክ አቅርቦት ጋር በተያያዘ ይነሱ የነበሩ ቅሬታዎችን የሚመልስ በመሆኑ ህብረተሰቡም ከግንባታው ጎን እንዲቆም ወይዘሮ ሙፈሪያት ጠይቀዋል፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አሸብር ባልቻ በበኩላቸው የወራቤ ኤሌክትሪክ ማከፋፈያ ጣቢያ ግንባታ ሲቦ ሀይብሮ በተሰኘ የቻይና ተቋም የሚገነባ እንደሚገነባና ግንባታውም በ12 ወራት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ተናግረዋል።
በዞኑ ውስጥ የሚገኙ መሰረተ ልማቶች በኤሌክትሪክ ኃይል እጦት ተጀምረው ባሉበት መቅረታቸውን አስታውሰው÷ ችግሩ እንዲቀረፍም ህብረተሰቡም በተደጋጋሚ ቅሬታ ሲያቀርብ መቆየቱን አስታውስዋል።
አሁን የሚገነባው የኤሌክትሪክ ማከፋፈያ ጣቢያ በዞኑ ለበርካታ ዓመታት የሚታዉን የኤሌትሪክ ኃይል መቆራረጥ ችግር በዘላቂነት እንደሚቀርፈውም ነው ዋና ስራ አስፈጻሚው የገለጹት፡፡
የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አሊ ከድር በበኩላቸው፥ የተለያዩ ኢንቨስትመንት አማራጮችን ወደ ከተማዋ ለመሳብ እና ለከተማዋ ሁለንተናዊ ዕድገት የማከፋፈያ ጣቢያው ድርሻ ከፍተኛ እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡
በጀማል ከድሮ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!