Fana: At a Speed of Life!

ትምህርት ሚኒስቴር የበይነ መረብ መማሪያ ስርዓትና ዲጂታል ቤተ መጻሕፍት አገልግት መስጠት ጀመረ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ትምህርት ሚኒስቴር የመረጃ፣ የተግባቦት እና ቴክኖሎጂ አጠቃቀም እንዲሁም የዲጂታል ቴክኖሎጂ አተገባበር ሥርዓትን ማሻሻል የሚያስችሉ መርሃ ግብሮችን ይፋ አድርጓል።
ሚኒስቴሩ ለተማሪዎች ይጠቅማሉ ብሎ ካዘጋጃቸው ፕሮግራሞች መካከል፥ የበይነ መረብ (ኦንላይን) መማሪያ ስርዓትን እና ዲጂታል ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት፣ መደበኛ እና አጋዥ መጻሕፍት፣ ተንቀሳቃሽ ምስሎች ይገኙበታል፡፡
አገልግሎቱም በክፍል፣ በትምህርት አይነት እንዲሁም በምዕራፍ በመምረጥ ለአጠቃቀም ቀላል ሆኖ መቅረቡን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የአካል ጉዳተኞችን እና ወደ ትምህርት ቤት መምጣት የማይችሉ ተማሪዎችን ችግር እንዲያቃልል ሆኖ የተዘጋጀ ሲሆን፥ ልዪ ተሰጥኦ ላላችው ተማሪዎችም የተመቸ ነው ተብሏል፡፡
በአሁኑ ወቅት ከ3 ሺህ በላይ የሚሆኑ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት የማስተማሪ ግብዓት በክፍል፣ በትምህርት አይነት እና በምዕራፍ ተከፋፍሎ ወደ ስርዓቱ ማስገባት የተቻለ ሲሆን፥ ግብዓቶቹን በነፃ በኢንተርኔት እና ከኢንተርኔት ውጪ በማውረድ መጠቀም እንደሚቻልም ተመላክቷል፡፡
በቀጣይ ለመጀመሪያ ደረጃ እና የቅድመ መደበኛ ተማሪዎች የዚሁ አግልግሎት ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.