Fana: At a Speed of Life!

ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያ በጫነ ተሽከርካሪ ላይ በደረሰ ፍንዳታ የሁለት ፖሊስ አባላት ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጎንደር ከተማ ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያ በጫነ ተሽከርካሪ ላይ በደረሰ ፍንዳታ የሁለት ፖሊስ አባላት ህይወት ማለፉን ፖሊስ አሳወቀ፡፡

የፍንዳታው መንስኤ እየተጣራ መሆኑን ያሳወቀው ፖሊስ፥ ፍንዳታው ከቦምብ ጋር የተያያዘ ሳይሆን እንዳልቀረም ገልጿል፡፡

የጎንደር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር አየልኝ ታክሎ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ ከጭልጋ መስመር ህገወጥ ጥይት የጫነ የደረቅ ጭነት ተሸከርካሪ በአዘዞ የፍተሻ ኬላ አምስተኛ ዋና ፓሊስ ጣቢያ በፖሊስ አበላት እየተፈተሸ ባለበት ወቅት ነው ፍንዳታው የደረሰው ።

በፍንዳታው ሁለት የፖሊስ አባላት ህይወታቸው ማለፉን የተናገሩት ኮማንደሩ፥ ሰባቱ ደግሞ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል ብለዋል።

በጣቢያው የነበሩ ሁለት ሲቪል ሰዎችም የፍንዳታው ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን፥ ወደ ሆስፒታል ተወስደው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡

የአዘዞና አካባቢው ማህበረሰብ ተጨማሪ ጉዳት እንዳይደርስ ላደረገው ትብብር ፖሊስ ምስጋና አቅርቧል፡፡

በምናለ አየነው

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.