Fana: At a Speed of Life!

ከአይሻ የንፋስ ሀይል ማመንጫ 40 ሜጋ ዋት ለማመንጨት ዝግጅት ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣የካቲት 18፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል እየተገነባ ካለው የአይሻ የንፋስ ሀይል ማመንጫ 40 ሜጋ ዋት ሀይል ለማመንጨት ዝግጅት መጠናቀቁ ተገለፀ፡፡
በውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ የተመራ ልዑክ የአይሻ የንፋስ ሀይል ማመንጫን ጎብኝቷል፡፡
በዚሁ ወቅት እንደተገለፀውም ሀይል ማመንጫው አጠቃላይ 48 ዩኒቶችን የሚይዝ ሲሆን፥ ከዚህ ውስጥ 32 ዩኒቶች ተተክለዋል ፡፡
ከ32ቱ ደግሞ 16ቱ ዩኒቶች ሀይል ለማመንጨት ዝግጁ መሆናቸው ተገልጿል።
አንዱ ዩኒትም 2 ነጥብ 5 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ሀይል ያመነጫል የተባለ ሲሆን፥ አጠቃላይ ስራው ሲጠናቀቅም 120 ሜጋ ዋት እንደሚያመነጭ ነው የተመለከተው።
የፕሮጀክቱ ሬዚደንት ኦፕሬሽን ተወካይ ኢንድሪስ ገዙ፥ የአይሻ የንፋስ ሀይል ማመንጫ ግንባታ በ18 ወራት ያልቃል ተብሎ ቢጀመርም በተለያዩ ምክንያቶች አራት አመት ፈጅቷል ብለዋል፡፡
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ፥ በመንግስት በኩል የኢነርጂው ዘርፍ ትኩረት እንደተሰጠው አንስተው የአይሻ የንፋስ ሀይል ማመንጫም የተጠቀሱት ችግሮች ተቀርፈውለት ወደ ስራ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
በፈቲያ አብደላ

 

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.