Fana: At a Speed of Life!

የነዳጅ ዋጋ እስከ መጋቢት 30 ድረስ ባለበት ይቀጥላል

አዲስ አበባ፣የካቲት 18፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግስት የነዳጅ ዋጋ ከየካቲት 19 እስከ መጋቢት 30 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ባለበት እንዲቀጥል መወሰኑን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ።

ውሳኔው ከቀላል ጥቁር ናፍጣ፣ ከባድ ጥቁር ናፍጣ እና ከአይሮኘላን ነዳጅ በስተቀር በሌሎች የነዳጅ ዓይነቶች መሸጫ ዋጋ ላይ ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑም ነው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ያስታወቀው።

ይህም የኢኮኖሚና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች በተረጋጋ ሁኔታ እንዲቀጥል ለማስቻል መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

እንደ ኢቢሲ ዘገባ በዓለም ገበያ የሚኖረውን የነዳጅ ዋጋ መነሻ በማድረግ እንደአስፈላጊነቱ ማስተካከያ ሊደረግ የሚችል መሆኑን የጠቆመው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ መንግስት የነዳጅ ምርት ከገዛበት ውድ ዋጋ በግማሽ ለህብረተሰቡ በሽያጭ እያስተላለፈ ይገኛል ብሏል።

በመሆኑም ህብረተሰቡ ምርቱን በከፍተኛ ቁጠባ የመጠቀም እንዲሁም የብዙሃን ትራንስፖርትን የመጠቀም ልምድ ሊያዳብርና በነዳጅ ምርቶች ግብይት ላይ የሚፈፀሙ ህገ ወጥ ተግባራትን በማጋለጥ ከፀጥታ አካላትጋር በትብብር ሊሠራ እንደሚገባ አሳስቧል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.