ክሮሽያ ኤምባሲዋን በኢትዮጵያ ለመክፈት ማቀዷን ገለጸች
አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ክሮሽያ ኤምባሲዋን በኢትዮጵያ ለመክፈት ማቀዷን ገለጸች።
አምባሳደር ደሚቱ ሀምቢሳ ከክሮሽያ የፖለቲካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል ፒታር ማሃቶብ ጋር በኢትዮጵያና ክሮሽያ መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ማጠናከር የሚያስችል ውይይት አካሂደዋል።
በወቅቱም ዳይሬክተር ጄኔራሉ ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር በማለም ኤምባሲዋን በኢትዮጵያ ለመክፈት ማቀዷን ገልጸዋል።
በውይይታቸውም በሀገራቱ መካከል ያለውን ግንኙነት ከፍ ወዳለ ደረጃ ለማሸጋገር እንዲሁም በባለብዙ ወገን መድረኮች ያለቸውን ትብብር አጠናክሮ ለማስቀጠል ከመግባባት ላይ መድርሳቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።