የሀገር ውስጥ ዜና

የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ መካሄድ ጀመረ

By Feven Bishaw

February 26, 2022

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ዛሬ ተጀምሯል።

ማዕከላዊ ኮሚቴው በተለያዩ ወሳኝ አገራዊ አጀንዳዎችና የፓርቲ ሥራዎች ላይ ተወያይቶ በቀጣይ ስለሚከናወኑ ተግባራት አቅጣጫ እንደሚያስቀምጥ ፓርቲው አስታውቋል፡፡

የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከቀናት በፊት ባካሄደው ስብሰባ በወሳኝ አገራዊ አጀንዳዎችና የፓርቲ ሥራዎች ላይ ተወያይቶ በቀጣይ ስለሚከናወኑ ተግባራት አቅጣጫ ማስቀመጡ ይታወሳል።