Fana: At a Speed of Life!

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሕክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ያሰለጠናቸውን 457 ተማሪዎች አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሕክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 457 ተማሪዎች አስመረቀ ፡፡

ኮሌጁ 383 በቅድመ-ምረቃ፣ 24 በማስተርስ እንዲሁም በሕክምና ስፔሻሊቲ 50 በድምሩ 457 ተማሪዎችን ነው እያስመረቀ የሚገኘው፡፡ ከተመራቂዎቹ መካከልም 187 ሴቶች መሆናቸው ታውቋል፡፡

ኮሌጁ ከተቋቋመበት ጀምሮ በቅድመ-ምረቃ 2 ሺህ 456፣ በድህረ-ምረቃ 805፣ በሕክምና ስፔሻሊቲ 219፣ በሶስተኛ ዲግሪ 6፣ በድምሩ 3 ሺህ 486 ተማሪወችን አስመርቋል።

የሕክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የሀገሪቱን የጤና ስርዓት ለማሻሻል፣ ለማህበረሰቡ ጥራት እና ተደራሽነት ያለው የሕክምና አግልግሎት መስጠት የሚችሉ ባለሙያዎችን በማፍራት የበኩሉን አስተዋፅኦ እያበረከተ መሆኑን ገልጿል፡፡

በአሁኑ ሰዓትም ኮሌጁ 2 ሺህ 363 ተማሪዎችን እያስተማረ እንደሚገኝ ከዩኒቨርሲተው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.