Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ በምስራቅ ባሌ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች 20 ሚሊየን ብር የሚያወጣ የዓይነት ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ በምስራቅ ባሌ ዞን በድርቁ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች 20 ሚሊየን ብር የሚያወጣ የዓይነት ድጋፍ አደረገ፡፡

የዓይነት ድጋፉ 2 ሺህ ኩንታል የምግብ ፍጆታ፣ 40 ሺህ ሊትር የምግብ ዘይት ፣ 20 ሺህ የቤት እንስሣት እና ሌሎች ሕጻናትና አዋቂዎች በምግብነት ሊጠቀሙባቸው የሚችሉ የተዘጋጁ የምግብ ግብዓቶች መሆናቸው ተመልክቷል፡፡

የምስራቅ ባሌ ዞን አስተዳዳሪ እሸቱ በቀለ የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ላደረገው ድጋፍ ምሥጋና አቅርበው ባንኩ ከዞኑ የተፈናቀሉ የኅብረተሰብ ክፍሎችን በመደገፍ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽዖ እያበረከተ ይገኛል ብለዋል።

ድጋፉ በዞኑ ለችግር ለተጋለጡ እንደ ሳዌና፣ ራይቱ፣ ዳዌ ሳራሪ እና ዳዌ ቃቻን ወረዳዎች ይውላል ተብሏል።

ባንኩ ላደረገው ድጋፍም የአካባቢቢው የሀገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት አባቶች ምሥጋና ማቅረባቸውን ከኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ አመልክቷል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.