Fana: At a Speed of Life!

ከ200 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ መድሃኒቶችንና የህክምና መሳሪያዎችን ላዳኑ የተቋሙን ሰራተኞች እውቅና ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት ደሴ ቅርንጫፍ ከ200 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ መድሃኒቶችንና የህክምና መሳሪያዎችን ላዳኑ የተቋሙን ሰራተኞች እውቅና ሰጠ፡፡

በኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት ደሴ ቅርንጫፍ አሸባሪዉ የትህነግ ሃይል ወደ ደሴ በገባበት ወቅት ሊያወድማቸው የሚችሉ 147 ሚሊየን ብር የሚገመቱ የህክምና ቁሳቁሶችን እና መድሃኒቶችን ቀድሞ በማሸሽ ማዳን ተችሏል፡፡

በወረራዉ ወቅትም ተቋሙን በፈረቃ በመጠበቅ እና የህዝብ አገልግሎት ሰጪ መሆኑን በማስረዳት ጭምር 65 ሚሊየን ብር የሚገመት ሃብትን ከውድመት መታደግ ችለዋል፡፡

የተቋሙ ሰራተኞች ባደረጉት የቅድመ መከላከል እና የመልሶ ማቋቋም ተግባር ከ230 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ሃብት ማዳናቸውን የተቋሙ ስራ አስኪያጅ አቶ እሸቴ ሹሜ ገልጸዋል፡፡

በዚህም በአደጋ መከላከሉ እና በጥበቃ የተሳተፉ ባለሙያዎች ፣ አጋር አካላት እና ተቋማት እውቅና ተሰጥቷቸዋል፡፡

በመርሃ ግብሩ የተገኙት የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት ምክትል ዳሬክተር አቶ ሰለሞን ንጉሴ ፥ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱን ከውድመት ለመታደግ ሰራተኞችና አጋር አካላት ላደረጉት ተሳትፎ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በተጨማሪም በመልሶ ማቋቋሙ ላይ እየተሰሩ ያሉ ሁለንተናዊ ተሳትፎ የሚደነቁ ናቸውም ብለዋል፡፡

በአለባቸው አባተ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.