በወልድያ በደረሰ የእሳት አደጋ የሦስት ቤተሰብ አባላት ህይወት አለፈ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በወልድያ በደረሰ የእሳት አደጋ የአባት ፣ የእናት እና የህጻን ልጅ ህይወት አለፈ፡፡
በከተማዋ በ06 ቀበሌ በተለምዶ ጎማጣ ተብሎ በሚታወቀው ሰፈር አካባቢ የካቲት 18 ለ19/2014 ዓ.ም ምሽት በደረሰ የእሳት አደጋ የአባት፣ እናት እና ህጻን ልጃቸውን ጨምሮ ለሞት ሲዳርግ ፥ ሦስት ሰዎች ደግሞ በቃጠሎው አደጋ ደርሶባቸዋል።
ሦስቱ ቁስለኞች በወልድያ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።
ፖሊስ የእሳት አደጋው መንስኤ እና በንብረት ላይ የደረሰውን አጠቃላይ ጉዳት በማጣራት ላይ እንደሆነ ከከተማው ኮሙኒኬሽን ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!