ወርሃ ጾሙ ለተፈናቀሉና በድርቁ ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ የምናደርግበት ሊሆን ይገባል- ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ወርሃ ጾሙ ለተፈናቀሉና በድርቁ ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ የምናደርግበት ሊሆን ይባል ሲሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ተናገሩ፡፡
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የዐቢይ ጾም መግባትን አስመልክተው ለመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያን ምዕመናን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በመልዕክታቸውም÷ በግጭቱና በድርቁ ለተጎዱ ወገኖች ካለን በማካፈል የችግሮቻቸው ተካፋይ መሆን ይገባል ብለዋል፡፡
ህዝበ ክርስቲያኑ ወርሃ ጾሙን ራሱን ኃይል ሰጪ ከሆኑ ምግቦች በመከልከል ብቻ ሳይሆን÷ ከጸብና ከጥላቻ በመራቅ ሊያሳልፈው እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡
የጾሙ ወቅት ምእመኑ ንስሃ የሚገባበት፣ ጥላቻን ከህሊናው የሚያስወግድበት ፍቅርን በመሻት ወደ እግዚአብሔር የሚቀርብበት ሊሆን እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡
በዚህ ጾም ህዝበ ክርስቲያኑ ስለሀገር እና ስለቤተክርስቲያን መፀለይ እንደሚገባውም በመልዕክታቸው አንስተዋል፡፡
በቅድስት ብርሃኑ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!