ቻይና ከሩሲያ በምታስገባው የስንዴ ምርት ላይ ጥላው የነበረውን ገደብ አነሣች
አዲስ አበባ፣ የካቲት 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና ከሩሲያ በምታስገባው የስንዴ ምርት ላይ ጥላው የነበረውን ገደብ ማንሳቷን አስታውቃለች፡፡
ቻይና ከሩሲያ በሚገባ የስንዴ ምርት ላይ ተጥሎ የቆየው ገደብ መነሳቱን ለሀገሪቱ አጠቃላይ የጉምሩክ አስተዳደር ያሳወቀች ሲሆን÷ አሁን ላይ ቤጂንግ ለሩሲያ የስንዴ ምርት አቅርቦት ሙሉ በሙሉ ክፍት ሆናለች፡፡
የቤጂንግ ውሳኔ ሩሲያ ከአውሮፓ ኅብረት እና ከአሜሪካ ከባድ የኢኮኖሚ ማዕቀብ እየተጣለባት ያለበት ወቅት እንደመሆኑ ለሩሲያ ኢኮኖሚ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ነው ዘገባው ያመላከተው፡፡
ቻይና ቀደም ሲል ከሩሲያ የሚገቡትን የስንዴ፣ የአትክልት እና ፍራፍሬ ምርቶች የዕፅዋት በሽታዎችን ስርጭት ለመግታት በሚል ወደ ሀገሪቱ እንዳይገቡ ከልክላ ነበር፡፡
በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ወደ ቤጂንግ ባደረጉት ጉብኝት÷ ቻይና ከሩሲያ የሚመጡ ምርቶችን እንዲገቡ መስማማቷን አር ቲ ዘግቧል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!