Fana: At a Speed of Life!

የሥራ ዕድል መፍጠር ጊዜ የሚሰጠው ጉዳይ አይደለም-አቶ ደስታ ሌዳሞ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሥራ ዕድል መፍጠር ጊዜ የሚሰጠው ጉዳይ አይደለም ሲሉ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ደስታ ሌዳሞ ተናገሩ፡፡
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የሥራ ዕድል ፈጠራ የስትሪንግ ኮሚቴ የ7 ወር አፈፃፀሙን ገምግሟል።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ በግምገማ መድረኩ ላይ እንደተናገሩት ፥ በክልሉ ሥራ የሚፈልጉ ወጣቶች በርካታ በመሆናቸው ወጣቱን ቀጥሮ ብቻ ስራ ማስያዝ ስለማይቻል የሥራ ዕድል መፍጠር ጊዜ የሚሰጠው ጉዳይ አይደለም ብለዋል።
ስለሆነም ወጣቶችን በተለያዩ አደረጃጀት ዘርፎች ማለትም በግብርና፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በትምህርትና በሌሎች ዘርፎች በማዋቀር ለወጣቶች ሥራ እድል መፍጠር ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
በክልሉ ያሉ ወጣቶችም መቀጠርን ብቻ የሥራ ዕድል ከማድረግ በመንግሥት በኩል የሚፈጠረውን ምቹ አጋጣሚዎችን በመጠቀም የግል ሥራዎችን መፍጠር እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.