Fana: At a Speed of Life!

በተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች ያለ ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ምዝገባ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች ያለ ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ምዝገባ በአቡዳቢ የኢፌዴሪ ኤምባሲ ተጀመረ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቅርቡ በመካከለኛው ምስራቅ ሃገራት ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር ውይይት ለማድረግ በተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች የስራ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል።

በወቅቱም የዜጎችን መብት ከማስከበር ረገድ የተለያዩ ጥያቄዎችን ለበተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች መንግስት አቅርበው ተቀባይነት ማግኘቱ ይታወሳል።

ከዚህ ውስጥ ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው ኢትዮጵያውያን የመኖሪያ ፈቃዳቸው እንዲስተካከልላቸው የሚጠይቀው አንደኛው ነው።

ስምምነቱን ለማስፈጸም እንዲረዳ በህገ ወጥ መንገድ በተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ምዝገባ በዛሬው እለት በአቡዳቢ የኢፌዲሪ ኤምባሲ እና በዱባይ ቆንስላ ጄኔራል ፅህፈት ቤት መጀመሩን ከኤምባሲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ምዝገባው እስከ መጋቢት 13 ቀን 2012 ዓ.ም ወይም እስከ ፈረንጆቹ ማርች 22 ቀን 2020 ድረስ እንደሚቆይም ገልጿል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.