Fana: At a Speed of Life!

በሶማሌ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች 31 ሚሊየን ብር የሚገመት ድጋፍ ተበረከተ

 

አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል በድርቅ በተጎዱ አካባቢዎች ለሚገኙ ጤና ተቋማት አገልግሎት የሚውል 31 ሚሊየን ብር የሚገመት የተለያዩ መድሃኒቶች፣ የተመጣጠነ ምግብ እና የህክምና ቁሳቁሶች ድጋፍ ተደርጓል።

በጤና ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሰሀረላ አብዱላሂ የተመራ ከጤና ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት የተውጣጣ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ቡድን በሶማሌ ክልል በድርቅ በተጎዱ አካባቢዎች ለሚገኙ ስድስት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል እና ስድስት ጤና ጣቢያዎች አገልግሎት የሚውል የመድሃኒት፣ የተመጣጠነ ምግብ እና የህክምና ቁሳቁሶችን አስረክቧል።

31 ሚሊየን ብር የሚገመት መድሃኒት፣ የተመጣጠነ ምግብ እና የህክምና ቁሳቁሶች በሁለት ዙር በክልሉ ጤና ቢሮ በኩል ወደ ጤና ተቋማት የሚደርስ ርክክብ መደረጉ ተገልጿል።

በቀጣይም በድርቅ ለተጎዱ የኦሮሚያ፣ ደቡብ ክልል እና ደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የምግብና መድሃኒት አቅርቦት እንደሚቀጥል ወ/ሮ ሰሀረላ መግለጻቸውን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.