የሀገር ውስጥ ዜና

የጣሊያን የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ምክትል ሚኒስትር አዲስ አበባ ገቡ

By Feven Bishaw

February 28, 2022

አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጣሊያን የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ምክትል ሚኒስትር ማሪና ሴሬኒ ለሦሰት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡

ምክትል ሚኒስትሯ በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ ከፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፥ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንንና ከሌሎች ባለስልጣናት ጋር ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።