በአርቲስት ኑሆ ጎበና የሙዚቃ ስራዎች አበርክቶ ላይ ያተኮረ አውደጥናት ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2014 (አፍ ቢ ሲ) በአርቲስት ኑሆ ጎበና የሙዚቃ ስራዎች ዙሪያ ያተኮረ አውደጥናት በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ተካሄደ፡፡
በመድረኩ አርቱስት ኑሆ ጎበና ለኦሮሞ ህዝብ ሙዚቃ እድገት ያበረከተው ሙያዊ አበርክቶ በተመለከተ በኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ቢሮ የኪነ ጥበብ አማካሪ በአቶ መሀመድ ቆጴ ሙያዊ ገለፃ ቀርቧል።
አርቲስቱ በስራዎቹ ስለ ኦሮሞ ህዝብ በመታገል ሙዚቃውን ከህዝባዊ ትግሉን ጎን ለጎን ያስክሄድ እንደነበር ነው አማካሪው የገለፁት።
በተለይም የኦሮሞን ህዝብ አንድነት በማጠናከር ረገድ ያበረከተው አስተዋፅኦ የማይተካ እንደነበር አብራርተዋል።
ከዚህም ባሻገር አርቲስቱ እስከ ዕለተ ሞቱ ድረስ ለኦሮሞ ሙዚቃ፣ ቋንቋ፣ ባህልና ዕድገት አስተዋፅኦ ሲያበረክት መቆየቱ ተመላክቷል።
በቀጣይም አርቲስቱ ለኦሮሞ ህዝብ የተጫወተውን ሚና የሚዘክሩ ስራዎች መስራት ይጠበቃል ተብሏል።
በአውደጥናቱ የአርቲስቱን ባለቤት ጨምሮ አርቲስት ኤለሞ አሊ፣ አርቲስት ሸንተማ ሹቢሳ እና አርቲስ አደም አሊ በተገኙበት ጥናታዊ ጽሑፍ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
በእዮናዳብ አንዱዓለም
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!