“ግንባታ ለሀገር አለኝታ” በሚል መሪ ቃል የኮንስትራክሽን የንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኮንስትራክሸን ባለስልጣን “ግንባታ ለሀገር አለኝታ” በሚል መሪ ቃል በሀገር አቀፍ ደረጃ በተመረጡ አራት ከተሞች ለማካሄድ ያቀደው የንቅናቄ መድረክ በድሬዳዋ ከተማ መካሄድ ጀመረ፡፡
የንቅናቄ መድረኩ በባለስልጣን መስርያ ቤቱ በሃገር አቀፍ ደረጃ በተመረጡ አራት ከተሞች ማለትም በድሬዳዋ፣ አዳማ፣ሃዋሳ እና ደሴ ሊካሄዱ ከታሰቡት ንቅናቄዎች አንዱ መሆኑን የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ማተቤ አዲስ ገልጸዋል፡፡
የድሬዳዋው የንቅናቄ መድረክ ለሁለት ቀናት የሚቆይ ሲሆን፥ በመድረኩ የሀረሪና የሶማሌ ክልሎች እንዲሁም የድሬዳዋ ከተማ መስተዳድርን የሶስት አመታት የግንባታ እና የኮንስትራክሽን ሁኔታ የሚዳስስ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
በምክክር መድረኩ እንደተዳሰሰው በሁለቱ ክልሎች እና በከተማ አስተዳደሩ የተሰሩ እና በመሰራት ላይ ያሉ የኮንስትራክሽን ስራዎች በተያዘላቸው ጊዜ እና በጀት ያለመጠናቀቅ እና የጥራት ችግሮች በተለይም በከተሞች እየተሰሩ ያሉ ግንባታዎች ማህበረሰቡን ማእከል ያላደረጉ እንደሆኑ እና መንገዶችም ተሰርተው እንዳለቁ ወዲያው ለብልሽት ይዳረጋሉ፡፡
የንቅናቄው አላማ የሚገነቡት ግንባታዎች በተያዘላቸው በጀት፣ ጊዜ እና ጥራት አንጻር ተገምግመው የተስተዋሉት ችግሮች እንዲቀረፉ ማስቻል እና በቀጣይ ውጤታማ የኮንስትራክሽን ግንባታ ስራዎችን ለመስራት ታሳቢ ያደረገ ነው ተብሏል፡፡
በግንባታው ዘርፍ የጥራት ጉድለትን ፣ የስነምግባር ግድፈትን እንዲሁም የግል ጥቅም አሳዳጅነትን ከዘርፉ በማላቀቅ ጥራት ያለው እና ደረጃቸውን የጠበቀ የግንባታ ዘርፍን በኢትዮጵ መገንባቱ አሰፈላጊ እንደሆነም በንቅናቄው መድረክ ላይ ተነሰቷል፡፡
በነሰሪ ዩሱፍ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን