Fana: At a Speed of Life!

ከደሴ ወደ ሰሜን ሸዋ ዞን በህገ ወጥ መንገድ ሊገባ የነበረ አንድ መትረየስና ከ7 ሺህ በላይ ጥይት ተያዘ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) መነሻውን ደሴ ከተማ አድርጎ ወደ አማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በህገ ወጥ መንገድ ሊገባ የነበረ አንድ መትረየስና ከ7 ሺህ በላይ የክላሽ ጥይት መያዙን የሚዳ ወረሞ ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
 
የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር በላይነህ ኃይሉ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት፥ የጸጥታ መዋቅሩ ሌሊት ላይ ባደረገው የኬላ ፍተሻ ህገ ወጥ የጦር መሳሪው በአይሱዙ መኪና ተጭኖ ወደ ሰሜን ሸዋ ዞን ሊገባ ሲል መያዙን አብራርተዋል፡፡
 
እንደ ሃላፊው ገለጻ፥ መራኛ ከተማ 01 ቀበሌ አባ ገሚስ የፍተሻ ጣቢያ በተደረገ ፍተሻ በመኪናው ግራና ቀኝ ብረት መሰል ሳጥኖች ሲከፈቱ ነው ህገወጥ የጦር መሳሪያው የተያዘው ።
 
በዚህም አንድ መትረየስ የጦር መሳሪያ እና ከ7 ሺህ በላይ የክላሽ ጥይት እንዲሁም 150 ጥይት መያዝ የሚችል የብሬል ሽልሻል መያዙን ተናግረዋል፡፡
 
በወንጀሉ የተጠረጠሩ አራት ግለሰቦችም በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው መሆኑን ዋና ኢንስፔክተሩ ጠቁመዋል፡፡
 
በአበበ የሸዋልዑል
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.