Fana: At a Speed of Life!

ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ ባለፉት 7 ወራት ከ3 ቢሊየን ብር በላይ ሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በገቢዎች ሚኒስቴር የምስራቅ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ባለፉት ሰባት ወራት ከ3 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር በላይ ሰበሰበ፡፡
 
ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ የ2014 በጀት ዓመት የ7 ወራት አፈጻሙን ከቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ ሰራተኞች ጋር ገምግሟል፡፡
 
የጽህፈት ቤቱ ሥራ አስኪያጅ አቶ ገዛኻኝ ታምሩ እንደገለጹት፥ በሰባት ወራት ውስጥ 2 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ ነው ከ3 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር በላይ የተሰበሰበው፡፡
 
በዚህም የእቅዱን 116 በመቶ በመፈጸም አበረታች ውጤት ማስመዝገብ መቻሉ ተመላክቷል፡፡
 
በቀሩት ጥቂት ወራት ውስጥ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን በማክሰም እንዲሁም ጥንካሬዎችን በማስቀጠል በበጀት ዓመቱ ለመሰብሰብ የታቀደውን ከ4 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ለማሳካት እንደሚሰራ መናገራቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.