Fana: At a Speed of Life!

በህገ ወጥ መንገድ ወደ ነቀምቴ ሊገባ የነበረ ከ5 ሺህ በላይ የክላሽ ጥይት ተያዘ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በህገ ወጥ መንገድ ወደ ነቀምቴ ከተማ ሊገባ የነበረ ከ5 ሺህ በላይ የክላሽ ጥይት መያዙን የቡኖ በደሌ ዞን ሰላምና ጸጥታ ጽህፈት ቤት ገለጸ፡፡
 
የዞኑ ሰላምና ጸጥታ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ክፍሌ ዘውዴ እንደገለጹት፥ ህገ ወጥ ጥይቱ የተያዘው በቡኖ በደሌ ዞን በደሌ ወረዳ ሃይሩፍ በተሰኘ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ላይ በተደረገ ፍተሻ ነው፡፡
 
ሃላፊው በዞኑ የህዝብን ሰላም የሚያውኩ አካሄዶችን እና የሸኔን እንቅስቃሴ ለመግታት ሁሉም ዜጋ የተቀናጀ ስራ እንዲሰራ ጥሪ ማቅረባቸውን ከኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.