Fana: At a Speed of Life!

ፋሲል ከነማና ዳሽን ቢራ የ136 ሚሊየን ብር የስፖንሰር ሺፕ ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2014(ኤፍ ቢሲ) የ2013 ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሻምፒዮኑ ፋሲል ከነማ ከዳሸን ቢራ ጋር የ136 ሚሊየን የስፖንሰር ሺፕ ስምምነት ተፈራርሟል፡፡

ሁለቱ ወገኖች ስምምንቱን ዛሬ በአዲስ አበባ ተፈራርመዋል።

ፋሲል ከነማ ስራ አስኪያጅ አቶ አብዮት ብርሀኑ ከፊርማው ስነስርዓት በኋላ እንደተናገሩት፥ ክለቡ ባለፋት አምስት ዓመታት ማሳካት የቻለውን ሁሉ ያሳካው ዳሽን ቢራ ከጎኑ በመኖሩ መሆኑን አንስተው ምስጋና አቅርበዋል።

ከፋሲል ከነማ ጋር በተለያዩ ገቢ ማሰባሰቢያ መርሀ ግብሮች ላይም በትብብር የሚሰራ ይሆናልም ብለዋል፡፡

የዳሽን ቢራ ህዝብ ግንኙነት ስራ አስኪያጅ አቶ አብርሃም ዘሪሁን በበኩላቸው፥ “ተቋም ያለ ህብረተሰብ ምንም ነው፣ ይህን ታሳቢ በማድረግ ባለፉት 5 ዓመታት ከፋሲል ከነማ ጋር ሰርተናል” ብለዋል።

“ፋሲል ከነማ በአጭር ጊዜ የሊጉ ሻምፒዬና መሆን ችሏል፤ ከዚህ ስኬት ጀርባ ዳሽን ቢራ ነበር፤ በቀጣይ 5 ዓመታትም እንዲሆን የምንፈልገው ይሄው ነው” ብለዋል።

ዳሽን ቢራ ባለፉት 20 ዓመታት በኅብረተሰብ አቀፍ አስተዋጽኦ ወደ 800 ሚሊየን ብር ወጪ ማድረጉም በመድረኩ ላይ ተጠቅሷል።

በሳምሶን ጥላሁን

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.