የሀገር ውስጥ ዜና

የኦዲፒ ማእከላዊ ኮሚቴ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ስብሰባውን አጠናቀቀ

By Tibebu Kebede

October 18, 2019

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኦዲፒ) ማዕከላዊ ኮሚቴ በዛሬው እለት ስብሰባውን አጠናቀቀ።

ማእከላዊ ኮሚቴው ለሁለት ቀናት በአዲስ አበባ ከተማ ሲያካሂድ የነበረውን ስብሰባ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ማጠናቀቁ ተገልጿል።

ማእከላዊ ኮሚቴው በስብሰባው የፓርቲውን እና የክልሉን መንግስት የስራ አፈፃፀም የገመገመ ሲሆን፥ በወቅታዊ ሀገራዊ እና ክልላዊ ጉዳዮች ላይም ተወያይቷል።

የፓርቲው የውስጥ አንድነት እና የፖለቲካ ፓርቲዎች ሪፎርምንም እንዲሁም እንደ ሀገር እና እንደ ክልል የተጀመሩ ለውጦች ዙሪያም ምክክር አድርጓል።