Fana: At a Speed of Life!

የንግድ ስርዓቱን በማዘመን ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚያስችል ስርዓት መዘርጋት እንደሚገባ ተጠቆመ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የንግድ ስርዓቱን በማዘመን ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚያስችል ስርዓት መዘርጋት እንደሚገባ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ገለጸ፡፡
የንግድና ቀጠናዊ ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ እንዳለው መኮንን÷ የተባበሩት መንግስታት የንግድና ልማት ኮንፈረንስ የአፍሪካ ዲቪዥን እና የልዩ ፕሮግራሞች ዳይሬክተር ፖል አኪውሚን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
የስራ ሃላፊዎቹ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እና ሀገራዊ የማምረት አቅምን ለማወቅ የሚያስችል ስርዓት በመዘርጋት በኩል እንደ ሀገር መሰራት ስለሚገባቸው ዐበይት ተግባራት ላይ መወያየታቸው ተገልጿል፡፡
የንግድ ስርዓቱን በማዘመን ዘመኑን የዋጀ የንግድ ስርዓት ለመዘርጋት መከናወን ስለሚገባቸው ጉዳዮች በስፋት መወያየታቸውን ከንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.