የሀገር ውስጥ ዜና

የሐረርና ድሬዳዋን የውሃ ችግር ለመቅረፍ ተጨማሪ ጉድጓዶችን መቆፈርና ከአጎራባች ክልሎች ጋር መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ

By Feven Bishaw

February 28, 2022

አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የውሃ መገኛ ቦታዎችን ለይቶ ጉድጓዶችን በመቆፈር፣ ከአጎራባች ክልሎችና ከከተማ አስተዳደሮች ጋራ በመነጋገርና ተቀናጅቶ በመሥራት ለውሃ አቅርቦት ችግር እልባት መፈለግ አስፈላጊ መሆኑን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጅነር ሀብታሙ ኢተፋ ገለጹ፡፡

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ከሐረርና ድሬዳዋ ከተሞች የውሃ አገልግሎት ሃላፊዎች ጋር በመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን አቅርቦት ላይ ያተኮረ ውይይት በድሬዳዋ ከተማ አካሂደዋል፡፡