Fana: At a Speed of Life!

አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ11 ምሑራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጠ።
ዩኒቨርስቲው ባወጣው መግለጫ አግባብነት ባላቸው የትምህርት ክፍሎች ተመርመሮ፣ በየኮሌጆች አካዳሚክ ጉባዔዎች ተፈትሾ፣ አጥጋቢ በሆነ መልኩ በባለሙያ ተገመግሞ በዩኒቨርስቲው ሴኔት ታይቶ እና ይሁንታ አግኝቶ የቀረበለትን የሙሉ ፕሮፌሰርነት መረጃ የተመለከተው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሥራ አመራር ቦርድ ለ11 ምሑራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ አፅድቋል።
በዚህም መሰረት፦
1. ዶ/ር ቁምላቸው የሺጥላ
2. ዶ/ር ሽመልስ አሰፋ
3. ዶ/ር መንግስቱ ለገሰ
4. ዶ/ር ጉታ ዘነበ
5. ዶ/ር ፋሲል አሰፋ
6. ዶ/ር ጥልዬ ፈይሳ
7. ዶ/ር ብሩክ ላምቢሶ
8. ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ
9. ዶ/ር ዘበነ ክፍሌ
10. ዶ/ር ተረፈ ደገፋ እና
11. ዶ/ር ንጉሴ ደዬሳን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ አፅድቋል።
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፕሮፌሰርነት ማዕረግ የሚሰጣቸው ምሑራን በመማር ማስተማሩ፣ በጥናትና ምርምር፣ በዩኒቨርስቲ ውስጥ አገልግሎት እንዲሁም በማህበረሰብ አቀፍና ሙያዊ አገልግሎት በዩኒቨርስቲው ሴኔት ሌጅስሌሽን መሰረት የሚጠበቅባቸውን አስተዋጽኦ ለተወጡ እና ለዓለም የዕውቀት ስርጸት መዳበር ስኬታማ አበርክቶ ላደረጉ መምህራን እና ተመራማሪዎች መሆኑን አስታውቋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.