Fana: At a Speed of Life!

የመከላከያ ኅብረት ትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ አባላት የምስጋና ዝግጅት አካሄደ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የመከላከያ ህብረት ትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ በስራቸው የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ አመራርና አባላቱ የእውቅናና የምስጋና ዝግጅት አካሄደ፡፡

በዝግጅቱም የመከላከያ ሰራዊት ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሰን ጨምሮ ከፍተኛ የሰራዊቱ አመራሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

ዋና መምሪያው በስሩ ለሚገኙ ኮሌጆችና አካዳሚዎች በስራ አፈፃፀማቸው የላቀ ውጤት ላሳዩና የመቆያ ጊዜያቸውን ለሸፈኑ አባላት የሜዳይና የማዕረግ ዕድገት ሰጥቷል፡፡

ተቋሙ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን የሚወድ ሙያዊ የሆነ ኢትዮጵያዊ ሰራዊት በመገንባት ላይ መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሰ ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ በስልጠና ላይ የሚገኙት የጥቁር አንበሳ የዕጩ መኮንን ሰልጣኞች በአስተሳሰብና በተግባር ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን የሚወዱና የሚያገለግሉ መሪ መኮንኖችን ለማፍራት እየተደረገ ላለው ጥረት ማሳያ ናቸው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ ለሀገር ያገለገሉ ባለውለታ መሪዎችን ያፈራ ተቋም መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

የዋና መምሪያው ክፍሎች ለሚጠብቃቸው ግዳጆች ክህሎትና ችሎታ ያላቸው ወታደራዊ አመራሮችን ለማፍራት የሚያደርጉትን ጥረት አጠናክረው እንዲቀጥሉ ማሳሰባቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

አሸባሪዎቹ የህወሓትና የሸኔ ቡድኖች ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር በማበር ሀገርን ለማሸበር ሞክረው በመላው ህዝብና በፀጥታ ሀይሎች ጥምረት መክሸፉን የተናገሩት ደግሞ የመከላከያ የህብረት ስልጠና ዋና መምሪያ አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይመር መኮንን ናቸው፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.