Fana: At a Speed of Life!

የዓድዋ ዜሮ ኪሎ ሜትር ፕሮጀክት ግንባታ 75 በመቶ ተጠናቋል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዳግማዊ ምኒሊክ አደባባይ አካባቢ እያስገነባ ያለው የዓድዋ ዜሮ ኪሎሜትር ፕሮጀክት ግንባታ 75 በመቶ መድረሱ ተገለጸ።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትላልቅ ፕሮጀክቶች ጽህፈት ቤት ምክትል ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ምሬሳ ልኬሳ እንደገለጹት÷ የዓድዋ ማዕከል ግንባታ እየተጠናቀቀ ሲሆን አጠቃላይ አፈጻጸሙም 75 በመቶም ደርሷል።
ግንባታው በ3 ነጥብ 3 ሄክታር መሬት ላይ እየተካሄደ መሆኑን ገልጸው÷ ግንባታው 11 ሕንፃዎችን ያካተተ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
በውስጡም ሙዚየም፣አምፊ ቴአትር፣ የቤት ውስጥ መዝናኛዎች፣ ግዙፍ አዳራሽ፣ እስከ 1ሺህ መኪኖች የሚይዝ የመኪና ማቆሚያ እና ሌሎች ክፍሎችንም መያዙን አብራርተዋል።
ማዕከሉ በ4 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በጀት ወጪ እየተገነባ መሆኑን ጠቁመው÷ ፕሮጀክቱ ዓድዋ ላይ ያገኘናቸው የሀሳብ እና የእውቀት ድሎችን የተጠቀምንበት ነው ብለዋ ኢንጂነር ምሬሳ፡፡
ፕሮጀክቱ ለከተማ አስተዳደሩ ብቻ ሳይሆን ለአገር ብሎም ለአህጉር ያለውን ከፍተኛ ዋጋም ለኢፕድ አስረድተዋል፡፡
ግንባታው ከታሪካዊ ፋይዳው ባለፈ በውስጡ በያዛቸው ክፍሎች በርካታ የሥራ ዕድል እንደሚፈጥር ብሎም ዋነኛ የቱሪስት ማዕከል እንደሚሆንም ምክትል ሥራ አስኪያጁ ገልጸዋል።
በአሁኑ ወቅት የግንባታው የመዋቅር (ስትራክቸራል) ሥራው በሙሉ መጠናቀቁን ጠቅሰው÷ የቀለም፣ የኤሌክትሮ ሜካኒካል፣ የኤሌክትሪክ፣ ጣሪያ የማልበስና የመሳሰሉት ሥራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
ግንባታውን በተቻለ መጠን በታቀደለት ጊዜ ለማጠናቀቅ እየተረባረብን ነው ሲሉም ገልጸዋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.