Fana: At a Speed of Life!

ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በመተከል ዞን ለሚገኙ ተፈናቃዮች ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የንፋስ ስልክ የላፍቶ ክፍለ ከተማ በመተከል ዞን በተፈጠረው የጸጥታ ችግር ለተፈናቀሉ ወገኖች 16 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ግምት ያለው ድጋፍ አስረከበ፡፡
የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባባሪያ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መኮንን ዘነበ እደገለጹት÷ ለተፈናቀሉ ዜጎቸ ድጋፍ ለማድረግ በተሰበሰበው ገንዘብ አልባሳትና ምግብ ነክ ድጋፍ ተደርጓል፡፡
አዲስ አበባ የሁሉም ዜጎች መኖሪያ እንደመሆኗ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ድጋፍ እያደረጉ እንደሆነ ገልጸው÷ ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መናገራቸውን ከመተከል ዞን ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የመተከል ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጋሹ ዱጋዝ በበኩላቸው÷ በቀጠናው በተፈጠረው አለመረጋጋት ተፈናቅለው የሚገኙ ዜጎች ወደ ነበሩበት ቀየ እስከሚመለሱ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡
በከተማ አስተዳደሩ የተደረገው ሰብዓዊ ድጋፍ በአንድነት ችግሮችን መወጣት እንደሚቻል ማሳያ እንደሆነ ገልጸው ለተደረገው ትብብር ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.