ከ219 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው የታካሚ አልጋዎች እየተሰራጩ ነው
አዲስ አበባ፣የካቲት 22፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጃፓን መንግስት ድጋፍ ከ219 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው በድጋፍ የተገኙ የታካሚ አልጋዎች እየተሠራጩ መሆኑ ተገለጸ።
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ከጃፓን መንግስት በድጋፍ የተገኙ ደረጃቸውን የጠበቁ ዘመናዊ የታካሚ አልጋዎችን ከጥር 20 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ በማሰራጨት ላይ እንደሆ የህክምና መሳሪያዎች ክምችትና ስርጭት ባለሙያ አቶ የቻለ ሽፈራው ተናግረዋል፡፡
በድጋፍ የተገኙት አልጋዎች 2 ሺህ 500 ሲሆኑ ÷ከእነዚህ ውስጥ 1 ሺህ 640 መሰራጨቱን አቶ የቻለ ገልጸው ቀሪዎቹ 860 አልጋዎች በመሰራጨት ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
ስርጭቱም በተቋሙ ቅርንጫፎች አማካኝነት ለአማራ ፣ለኦሮሚያ፣ ለሀረሪ፣ለሲዳማ፣ ለደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች፣ ለሶማሌ ክልሎች፣ ለድሬደዋ ከተማ መስተዳደር፣ ለአዲስ አበባ ጤና ቢሮ እንዲሁም ለዩኒቨርሲቲ ሆስፒታሎች እና በቀጥታ ለጤና ተቋማት ስርጭት መካሄዱን ባለሙያው ገልጸዋል፡፡
በቀጣይ ለቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ ለጋምቤላና ለአፋር ክልሎች ስርጭት የሚካሄድ ሲሆን ÷በአጠቃላይ 219 ሚሊየን 594 ሺህ 650 ብር ዋጋ እንዳለቸው የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!