የላሙ ወደብ ፕሮጀክት ቀጠናዊ ትስስርን የሚያጠናክር መሆኑ ተገለፀ
በኬኒያ የኢትዮጵያ አምባሳደርና ባለ ሙሉ ስልጣን መለስ አለምን በመከል በዝግጅቱ ንግግር ያደረጉት አቶ ሂባሞ አያሌው፣ የላሙ ወደብ ፕሮጀክት ቀጠናዊ ትሰስርን የሚያጠናክር የኢኮኖሚ ልማት ፕሮጀክት መሆኑን ተናግረዋል።
ፕሮጀክቱ ድንበር ተሻጋሪ ንግድ እና ኢንቨስትመንቶችን ለማስተዋወቅ ሚናው ከፍተኛ መሆኑን የአምባሳደሩ ተወካይ ገልፀዋል፡፡
በመሆኑም ኢትዮጵያ የላሙ ወደብ ፕሮጀክትን ለማጠናከር እና ለምስራቅ አፍሪካ ህዝቦች አጠቃላይ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ለውጦችን ለማፋጠን የሚደረገውን ጥረት እንደምታግዝ ተወካዩ ገልፀዋል፡፡
የላሙ ወደብ ተደራሽነትን ማሰፋትና አፍሪካን በመሰረተ ልማት ለማፅናት በሚል ርዕስ 7ኛው የአፍሪካ የመሠረተ ልማት ፕሮግራም ሳምንት ዝግጅት በኬንያ በመካሄድ ላይ መሆኑን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!