Fana: At a Speed of Life!

በጋምቤላ ክልል የውስጥና ድንበር ዘለል ወንጀሎችን በመከላከል ሰላምን ለማስጠበቅ በትኩረት እየተሰራ ነው- የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን

አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል የውስጥና ድንበር ዘለል ወንጀሎችን በመከላከል ሰላምን ለማስጠበቅ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።
የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች በአቦቦ ወረዳ የዘረፉትን የቀንድ ከብቶች በማስመለስ በታጣቂዎቹ ላይ እርምጃ መወሰዱንም ኮሚሽኑ ገልጿል።
ክልሉ ከደቡብ ሱዳን ጋር ሰፊ የድንበር ወሰን ያለው ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ተደጋጋሚ ጥቃት ሲደርስ መቆየቱን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር አቡላ ኡቦንግ ተናግረዋል፡፡
የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች ትናንት ከቀኑ 7:00 ሰዓት አካባቢ በአበቦ ወረዳ መንደር 11 እና መንደር 12 220 የቀንድ ከብቶችን ዘርፈው መውሰዳቸውን አስታውቀዋል።
የክልሉ መንግስት የፀጥታ ሀይሉን በማደራጀት በወሠደው እርምጃ 215ቱን የቀንድ ከብቶች ማስመለስ ሲቻል ሁለት የታጣቂ ቡድን አባላት ላይ እርምጃ ተወስዷልም ነው ያሉት።
የፀጥታ ሀይሉ በሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች ላይ አስፈላጊውን እርምጃ ለመውሰድ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝም አስረድተዋል።
በጎግ ወረዳ ኡቦዋ ቀበሌ ከታጣቂ ቡድኑ ጋር በተደረገው የተኩስ ልውውጥ የሰው እና የእንስሳት ህይወት ማለፉ ተገልጿል፡፡
በክልሉ ዘላቂ ሰላምን ለማስፈንና የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች የሚያደርሱትን ጥቃት ለመከላከል ለሚደረገው ጥረት ስኬታማነት የማህበረሰቡ ድጋፍና ተሳትፎ እንደሚያስፈልግ ኮሚሽነር አቡላ ጥሪ ማቅረባቸውን ከክልሉ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.