Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን ለመቋቋም ለታዳጊ ሀገራት የገንዘብ ድጋፍ እንዲደረግ ጥሪ አቀረበች

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 22 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን ለመቋቋም ለታዳጊ ሀገራት ዘላቂ የገንዘብ ድጋፍ እንዲደረግ ጥሪ አቀረበች።
የኢፌዴሪ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ጌታሁን ጋረደው በኬንያ እየተካሄደ ባለው የተመድ የአየር ንብረት ጉባኤ ላይ እየተሳተፉ ነው።
በዚህ ወቅትም ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የአየር ንብረት ለውጥ እያደረሰ ያለውን ተፅዕኖ ለመቋቋም ለታዳጊ ሃገራት ዘላቂነት ያለው የገንዘብ ድጋፍ ሊያደርግ ይገባል ብለዋል።
አያይዘውም የአየር ንብረት ጥበቃ አጀንዳን በብሄራዊ እና ዓለም አቀፍ የፖሊሲ መድረኮች ላይ ማካተት ያለውን ፋይዳ በተመለከተ አጽንኦት ሰጥተዋል።
ከዚህ ባለፈም አስፈላጊውን የገንዘብ ድጋፍና የቴክኖሎጂ ሽግግር በማድረግ የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋሙ ፖሊሲዎችን ተግባራዊ ለማድረግ ተጨባጭ እርምጃ መውሰድ ያስፈልጋልም ነው ያሉት።
በኢትዮጵያ በ2025 የተያዘውን እቅድ ለማሳካትና የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን ለመቋቋም እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎችን በተመለከተም ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ ዘላቂ የልማት ግቦችን ተግባራዊ ለማድረግ ያላትን ቁርጠኝነት አስረድተዋል።
ነገ የሚጠናቀቀው ጉባኤ ከአካባቢ ጥበቃ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ላይ በመምከር የተለያዩ ውሳኔዎች እንደሚተላለፉበት ይጠበቃል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.