Fana: At a Speed of Life!

ሚሲዮኑ 139 ዜጎች ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በህገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ተታለው ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመጓዝ የኬንያን ድንበር በህገወጥ አቋርጠው የገቡ 139 ኢትዮጵያውያንን ሚሲዮኑ በምህረት ክሳቸው ተቋርጦና ከእስር ቤት ተፈተው ወደ ሀገራቸው እንዲገቡ ድጋፍ አድርጓል።

ኢትዮጵያውያኑ በኪያምቡ፣ ጊጊሪ፣ ፓንጋኒ፣ ጆጎ፣ ቡሩቡሩ እና ዳንዶራ እስር ቤቶች በእስር ከአንድ እስከ ዘጠኝ ወር ድረስ የቆዩ ናቸው።

ሚሲዮኑ ከኬንያ ወንጀል ምርመራ ዳይሬክቶሬት ጋር በቅርበት ሲሰራ የቆየ ሲሆን ÷ቀደም ሲልም በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ዜጎች ከእስር ተለቀው ወደ ሀገራቸው እንዲገቡ ድጋፍ ማድረጉ ን ከኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.