በመዲናዋ ለሚከበረው 126ኛው የአድዋ ድል በዓል ለተሸከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ይፋ ሆኑ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 126ኛው የአድዋ ድል መታሰቢያ በዓል በአዲስ አበባ ሲከበር የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይከሰት አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገድ እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
የአድዋ ድል 126ኛ የድል መታሰቢያ በዓል የካቲት 23 ቀን 2014 ዓ/ም ፒያሳ በሚገኘው ዳግማዊ ሚኒልክ አደባባይ እና አዋሬ አካባቢ በሚገኘው አድዋ ድልድይ ዙሪያ በደማቅ ስነ-ስርዓት ይከበራል፡፡
በዓሉን አስመልክቶ በምኒሊክ አደባባይ የሚካሄደው ፕሮግራም እስከሚጠናቀቅ
በቸርችል ጎዳና በቴዎድሮስ አደባባይ ወደ ዳግማዊ ምኒሊክ አደባባይ የሚወስደው መንገድ ባንኮ ዲሮማ መብራት
ከአራት ኪሎ በራስ መኮንን ወደ ዳግማዊ ምኒሊክ አደባባይ የሚወስደው መንገድ ራስ መኮንን ድልድይ
ከመነን አካባቢ እና የካቲት 12 ሆስፒታል በአፍንጮ በር ወደ ዳግማዊ ምኒሊክ አደባባይ የሚወስደው መንገድ አፍንጮ በር
ከእሪ በከንቱ በኤሌክትሪክ ህንፃ ወደ ዳግማዊ ምኒሊክ አደባባይ የሚወስደው መንገድ ደጎል አደባባይ
ከአዲሱ ገበያ በሰሜን ሆቴል ወደ ዳግማዊ ምኒሊክ አደባባይ የሚወስደው መንገድ ሰሜን መብራት
ከመርካቶ በአቡነ ጴጥሮስ ወደ ዳግማዊ ምኒሊክ አደባባይ የሚወስደው መንገድ ደጃዝማች ሀብተጊዮርጊስ ድልድይ
ከእንቁላል ፋብሪካ በዮሃንስ ቤተክርስቲያን ወደ ዳግማዊ ምኒሊክ አደባባይ የሚወስደው መንገድ ዮሃንስ መብራት ላይ ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ፡፡
በተመሳሳይ አድዋ ድልድይ አካባቢ ለሚከናወነው ፕሮግራም
ከመገናኛ በሲግናል ወደ አድዋ ድልድይ ድንበሯ ሆስፒታል መታጠፊያ
ከካዛንቺ በመለስ ዜናዊ ፋውንዴሽን ወደ ሴቶች አደባባይ የሚወስደው መንገድ ካዛንቺስ መታጠፊያ
ከእንግሊዝ ኤምባሲ ባልደራስ ኮንደሚኒዬም ወደ አድዋ ድልድይ እንግሊዝ ኤምባሲ ጋር
ከቀበና በአዋሬ ወደ አድዋ ድልድይ የሚወስደው ቤሌኤር መብራት
ከፓርላማ መብራት ወደ አዋሬ የሚወስደው መንገድ ፓርላማ መብራት
ከካዛንቺስ ወደ አድዋ ድልድይ የሚወስደው መንገድ እንደራሴ መታጠፊያ
ከዘሪሁን ህንፃ ወደ አድዋ ድልድይ የሚወስደው መንገድ ዝግጅቱ እስከሚጠናቀቅ ለጊዜው
ለተሽከርካሪ ዝግ መሆናቸውን አሽከርካሪዎች ተገንዝበው የትራፊክ ፖሊስ አባላት በሚጠቁሙት አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቃል፡፡
ዳግማዊ ምኒሊክ አደባባይ የሚከናወነው ፕሮግራም ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ከንጋቱ 12፡00 በተመሳሳይ አድዋ ድልድይ አካባቢ ለሚካሄደው ፕሮግራም ከዛሬ የካቲት 22 ቀን 2014 ዓ/ም ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ጀምሮ ለአጭርም ሆነ ለረጅም ሰዓት ተሽከርካሪን አቁሞ መሄድ ክልክልመሆኑም ተመላክቷል፡፡
የበዓሉ አዘጋጅ ኮሚቴ ከአንድ ሳምንት ቀደም ብሎ የበዓሉን አከባበር አስመልክቶ ለፀጥታ የጋራ ግብረ ባሳወቀው መሰረት የፀጥታ አካላት ዝግጅታቸውን አጠናቀው ወደ ስራ መግባታቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልፆል፡፡
በዓሉን ለመታደም ወደ ስፍራዎቹ የሚመጡ ታዳሚዎች ለጋራ ደህንነት ሲባል ፍተሻ መኖሩን ተገንዝበው ለፀጥታ አካላት ተባባሪ እንዲሆኑ ጥሪ ቀርቧል፡፡
ህብረተሰቡ ለጸጥታው አጠራጣሪ የሆኑ ነገሮች ሲያጋጥሙት ወይም የፖሊስ አገልግሎትን ማግኘት ሲፈልግ በ011-1-11-01-11 ወይም በነፃ ስልክ መስመር 991 መጠቀም እንደሚችል ፖሊስ አስታውቋል፡፡