Fana: At a Speed of Life!

የወልቃይት ጠገዴ ትግል የአማራን ትግል ቅርፅ ያስያዘ በመሆኑ የማንነት መለኪያ ተደርጎ ይወሰዳል- ርእሰ መሥተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የወልቃይት ጠገዴ ትግል የአማራን ትግል ቅርፅ ያስያዘ በመሆኑ የማንነት መለኪያ ተደርጎ ይወሰዳል ሲሊ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ ተናገሩ፡፡
የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ ወጣቶች ከአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ ጋር ተወያይተዋል፡፡ በውይይቱ፥ ወጣቶቹ በተዘዋወሩበት አካባቢ ሁሉ አማራዊ አንድነትን አጠንክረው መመለሳቸው ተብራርቷል፡፡
የጉብኝቱ ዓላማም የወልቃይት ጠገዴ ወጣቶች ባህላቸውንና እሴታቸውን ለሌሎች የአማራ አካባቢዎች እንዲያጋሩና እነርሱም የሌሎች አካባቢዎችንም እንዲያውቁ ማድረግ መሆኑ በምክክሩ ተመላክቷል፡፡
የአማራ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ኃላፊ ጋሻው ተቀባ እንደተናገረው፥ የወልቃይት ጠገዴ አማራ ሕዝብ ነፃነቱን በልጆቹ መስዋእትነት አረጋግጧል፡፡ የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ ወደ ቀደመ ማንነቱ እንዲመለስ ከፍተኛ ትግል ሲያደርግ እንደነበርም ገልጿል።
የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳደር ዶክተር ይልቃል ከፋለ ባደረጉት ንግግር እንደገለጹት÷ “የክልላችሁን አካባቢ በስኬት ጎብኝታችሁ በመገናኘታችን እንኳን ደስ ያለን፤ ሽፍታውና ዘረኛው የትህነግ ቡድን የአማራን ማኅበረሰብ ከአማራ ለመለየትና ከራሱ ጋር ለማቀላቀል የፈፀመው ወንጀል ታሪክ አይረሳውም” ብለዋል፡፡
የአማራ ህዝብ ሁሉንም በሰላም ለመፍታት ጥረት ማድረጉን ያስታወሱት ርዕሰ መስተዳድሩ፥ ግፉ ሞልቶ ሲፈስስ ግን የአማራ ህዝብ መነሳቱን ተናግረዋል ።
በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ ዞን ብዙ ችግር እንዳለ ገልጸው፥ የክልሉ መንግሥት መፍትሔ ለመስጠት የሚችለውን ሁሉ እያደረገ ነው ብለዋል፡፡ የአካባቢው ወጣቶች የወልቃይት ጠገዴ የመሠረተ ልማት ችግር አግባብ ባለው መንገድ እንዲፈታ እንደሚሠሩም ጠይቀዋ፡፡
ወልቃይት እንኳን ለራሱ ለሌሎች አካባቢዎች የሚተርፍ እምቅ አቅም ያለው መሆኑን ገልጸው፥ ወልቃይትን የልማት ምድር እናደርገዋለን ብለዋል፡፡ የክልሉ መንግሥት በወልቃይት የመንግሥት መዋቅር እንዲጠናከር እና ሕጋዊ እልባት እንዲያገኝ ይሠራልም ነው ያሉት።
አንድነታችን ከተጠናከረ ሊለያየን የሚችል አንድም ኃይል የለም፤ ተደራጁ የክልሉ መንግሥት ያግዛል፤ በጥቃቅን ችግር እንዳትበገሩ ማለታቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.