Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው ሸኔ በምዕራብ ሸዋ ዞን 647 ንጹሃን ዜጎችን ሲገድል፥ በ1 ሺህ 252 ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት አድርሷል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ሸኔ በምዕራብ ሸዋ ዞን እስካሁን የ647 ንጹሃን ዜጎችን ህይወት ሲያጠፋ፥ 26 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር በላይ በሚገመቱ የልማት ስራዎች ላይ መስተጓጎል መፍጠሩን የኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ገለጸ፡፡
 
ከቢሮው ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው፥ የምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ አመራሮች በልማት ስራዎች እና በጸጥታ ጉዳዮች ዙሪያ ከአባ ገዳዎች እና የአገር ሽማግሌዎች ጋር ተወያይተዋል፡፡
 
በዞኑ የብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ግርማ ኃይሉ ለውይይት መድረኩ ባቀረቡት ጽሁፍ÷አሸባሪው ሸኔ በምዕራብ ሸዋ ዞን እስካሁን 647 ንጹሃን ዜጎችን ሲገድል፥1 ሺህ 252 ሰዎች ላይ ደግሞ የአካል ጉዳት ማድረሱን ገልጸዋል፡፡
 
አሸባሪው ቡድን ከ85 ሺህ በላይ የሚሆኑ አባዎራዎችንም ከመኖሪያ ቀያቸው እንዳፈናቀለም በጽሁፉ ተጠቁሟል፡፡
 
በተጨማሪም 26 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር በላይ በሚገመቱ የልማት ስራዎች ላይ መስተጓጎል መፍጠሩን ነው አቶ ግርማ ያብራሩት፡፡

በተመሳሳይ በምስራቅ ሸዋ ዞን ወረ ጃርሶ ወረዳ አሸባሪው ሸኔን ለማጽዳት የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ መቀጠሉን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

የሽብር ቡድኑን ከአካባቢው ለማጽዳትም ከመከላከያ ሰራዊት፣ ከኦሮሚያ ልዩ ኃይል አና ፖሊስ እንዲሁም ከአካባቢው ሚሊሻ ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ነው ከሚሽኑ የገለጸው፡፡

 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.