አቶ ደመቀ መኮንን ጅግጅጋ ገቡ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የተመራ የልዑካን ቡድን ዛሬ ማለዳ ጅግጅጋ ገባ ።
ልዑኩን የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኢብራሒም ኡስማን እና የክልሉ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በጅግጅጋ ገራድ ዊልዋል አየር ማረፍያ ተገኝተው አቀባበል አድርገውለታል ።
የልዑካን ቡድኑ አባላት ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጋር በድርቁ አሁናዊ ሁኔታ ላይ ይወያያሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከሶማሌ ብዙሃን መገናኛ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!