Fana: At a Speed of Life!

የተለያዩ አገራት ኤምባሲዎች ለዐድዋ ድል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የሚገኙ የተለያዩ አገራት ኤምባሲዎች ለዐድዋ ድል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ፡፡

በኢትዮጵያ የሩሲያ ኤምባሲ ለወንድም የኢትዮጵያ ህዝብ እና መንግስት ለ126 ኛው የዐድዋ ድል በዓል እንኳን አደረሳችሁ ብሏል፡፡

ድሉ የኢትዮጵያን ሉአላዊነት ያጸና እና በውስጥ እና በውጭ ፖሊሲዎቿ ጭምር አልበገር ባይነቷን ያሳየ እንደሆነም ነው በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ተርክሂን የገለጹት፡፡

የዐድዋ ጦርነት ያለምንም ማጋነን በአፍሪካ በቅኝ ግዛት ለነበሩ ሁሉ ከቅኝ ግዛት ቀንበር ነፃ ለመውጣት ባደረጉት ትግል መሪ ኮከብ እንደነበርም አመላክተዋል።

ድሉ በኢትዮጵያ እና ሩሲያ ግንኙነት መመስረት ሂደት ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ መሆኑም ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ በበኩሉ ለመላው ኢትዮጵያውያን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.