Fana: At a Speed of Life!

ዐድዋ የጥቁር ሕዝቦች የነጻነት ፋና እና የሰዎች እኩልነት ምልክትና ምሳሌ ነው – አቶ ዣንጥራር አባይ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 23 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዐድዋ የጥቁር ሕዝቦች የነጻነት ፋና፣ የነጮችን የዘመናት የበላይነት የገታ፣ የሰዎች እኩልነት ምልክትና ምሳሌ የኢትዮጵያውያን አኩሪ ገድል ውጤት መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ዣንጥራር አባይ ተናገሩ።

ምክትል ከንቲባው በ126ኛው የዐድዋ ድል በአል ላይ በመገኘት መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመልዕክታቸውም “ኢትዮጵያውያን የምንኮራበት የረጅም ዘመናት የሀገረ መንግስት ታሪክ እና ልምድ ባለቤት የምንናገረው እና የምንተርከው ብዙ ድንቅ ታሪክና እሴት ያለን ህዝቦች ነን” ብለዋል።

አባቶቻችን ለሀገራቸው ኩራት ሲዋደቁ የውስጥ ችግሮቻቸውን ዋጥ አድርገው መጀመሪያ ኢትዮጵያ ብለው በአንድ ላይ በመትመም እንደነበርም አስታውሰዋል።

የዘንድሮው የዐድዋ ድል በዓል ዳግም አድዋዊ በሆኑ አንጸባራቂ ኢትዮጵያዊ ድሎች አሸብርቆ የሚከበር የድል በዓል መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

የዐድዋ ድል ፍትህን የሚያሳይ ነው ያሉት ምክትል ከንቲባው፥ ስለ ዐድዋ ስናስብ ጥንካሬያችንና አንድነታችነታችን ከፍ ይላል ብለዋል፡፡

የኦሮሚያ ምክትል ርእሰ መስተዳድር አወሉ አብዲ በበኩላቸው ÷ የዐድዋ ድል በአል ለኢትዮጵያ እንዲሁም ለመላው የጥቁር ህዝቦች የነፃነት ጮራ የፈነጠቀ መሆኑን አውስተዋል።

አያቶቻችን ወደጦር ግንባር በመሔድ ድል በማድረግ ሀገራችንን አቆይተዋል ያሉት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ፥ በተሰማራንበት መስክ ለእድገትና አንድነት መጠንከርን ከዐድዋ መማር እንደሚገባ አንስተዋል።

በዓለማየሁ ገረመው እና በቅድስት ተስፋዬ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.