Fana: At a Speed of Life!

ዶ/ር ይልቃል ከፋለ ትውልዱ እንደ ዐድዋ ጀግኖች ዘመንን የሚሻገር ሕያው ስራ ሊሰራ እንደሚገባ ገለጹ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ትውልዱ እንደ ዐድዋ ጀግኖች ዘመንን የሚሻገር ሕያው ስራ ሊሰራ እንደሚገባ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ ተናገሩ።

126ኛው የዐድዋ ድል በዓል በባህር ዳር ከተማ በድምቀት ተከብሯል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በዚህ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት በዓሉ መላው ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ የዐድዋ ድል ጮራ ለፈነጠቀላቸው ጥቁር ህዝቦች ሁሉ የደስታ ብስራት ቀን ነው ብለዋል።

በዓሉ አባቶች በኢትዮጵያዊ ልበ ሙሉነትና አንድነት እብሪተኛ ነጭን ያንበረከኩበት፣ ለዛሬዋ ኢትዮጵያ ፅኑ መሠረት እና ለትውልዱም የኩራት ቀን መሆኑን አስረድተዋል።

ትውልዱ እንደ አባቶቹ ዘመን የሚሻገሩ ተግባራት ላይ በህብረት የመቆምን ውርስ መላበሱን የተናገሩት ርዕሰ መስተዳድሩ ፥ የታላቁ ህዳሴ ግድብን ጨምሮ ሀገራዊ እሳቤዎች ላይ እየታየ ያለው የትውልዱ ቁርጠኝነት ለዚህ ማሳያ መሆኑን ጠቅሰዋል።

“ዐድዋን ያለ ንጉሡ ዳግማዊ አፄ ምኒልክ እና ያለ እቴጌ ጣይቱ ማሰብ አይቻልም” ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ መሪዎቹ ሀገርን ለድል የማስተባበርና ለሀገር በአንድነት የመቆምን ትርጉም ለትውልዱ በማውረሳቸው ሲወደሱ ይኖራሉ ማለታቸውን ከከተማው ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.