Fana: At a Speed of Life!

የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን ከነገ ጀምሮ ያካሂዳል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ምክር-ቤት ከነገ ጀምሮ የ3ኛ የስራ ዘመን 1ኛ አመት 50ኛ መደበኛ ጉባኤን ያካሂዳል፡፡

የምክር ቤቱ አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ ፈትህያ አደን የምክር-ቤቱን 50ኛ መደበኛ ጉባኤ አስመልክቶ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደገለጹት፥ ምክር ቤቱ በሁለት ቀናት ቆይታው የአስተዳደሩን የአስፈፃሚ አካላት የ6 ወር የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ተወያይቶ እንደሚያፀድቅ ገልፀዋል።

እንዲሁም የሚቀርብለትን የተለያዩ ሹመቶች ያፀድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ አስታውቀዋል፡፡

የድሬዳዋ አስተዳር ምክር ቤት ከህዝብ የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ ከምስረታው ጀምሮ ዘርፈ-ብዙ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ የገለፁት ወይዘሮ ፈትህያ በዚህም የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴዎች የመስክ ምልከታ፤ የክትትልና ቁጥጥር ስራዎች መሰራታቸውን ጠቁመዋል፡፡

በተሾመ ኃይሉ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.