የክልልና የፌደራል መንግስታት በድርቅ የተጎዱ ወገኖችና እንስሳቶቻቸውን የመታደግ ስራ አጠናክረው ይቀጥላሉ – አቶ ደመቀ መኮንን
አዲስ አበባ፣ የካቲት 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የክልልና የፌደራል መንግስታት በድርቅ የተጎዱ ወገኖችና እንስሳቶቻቸውን የመታደግ ስራ አጠናክረው ይቀጥላሉ ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ገለጹ፡፡
አቶ ደመቀ መኮንን እና የልዑካን ቡድናቸው በድርቁ ምክንያት ከአምስት ዞኖች የቤት እኖስሳቶቻቸውን ይዘው በፋፈን ዞን ወደ ሐሮሬስ ወረዳ የተፈናቀሉ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተመልክተዋል ።
በሐሮሬስ ወረዳ የሚገኙ የድርቅ ተፈናቃዮች በአሁኑ ወቅት ያሉበትን ሁኔታ የገለፁላቸው ሲሆን ፥ የወረዳው ማሕበረሰብ ያለውን ውሐና የእንሰሳት መኖ እየሰጣቸው ቢሆንም አሁን ለይ ካለው የፍላጎት መጠን መጨመር ጋር ተያይዞ ከአቅም በላይ በመሆኑ መንግስት የውሃና የመኖ ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ጠይቀዋል ።
አቶ ደመቀ መኮንን የድርቅ ተጎጅዎችን ያሉበትን ሁኔታ ለመመልከት መገኘታቸውን ገልፀው ፥ የሶማሌ ክልል ሰፊ የእንስሳት ሐብት ያለበት ህብረተሰብ በመሆኑ በክልሉም በፌደራል መንግስትም በድርቅ ለተጎዱ ወገኖችና እንስሳቶቻቸውን የመታደግ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
አክለውም በድርቁ ምክንያት የሰው ህይወት እንዳይጠፋ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው ፥ በቀጣይም ድርቁ በተከሰተባቸው አካባቢዎች በክልሉና በፌደራል መንግስቱ የጋራ ትብብር የውሃና አቅርቦትና የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ ላይ በትኩረት እንደሚሰራ ማስታወቃቸውን ከሶማሌ መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!